Tip:
Highlight text to annotate it
X
ቪሽኑጃን:ፕራብሁፓድ:አምላክ ኦሪጂናሉ ፈጣሪ እና መነሻ እንደሆነ ተናግረሃል:
ሆኖም እያለ:ሰዎች ይህን ፈጣሪ ማን እንደሆነ ሳያውቁ:እንዴት ብለው ነው ማን እንደሚቆጣጠራቸው ሊረዱት የሚችሉት:
ማንም ሰው ክርሽናን ስለማያውቅ እና እርሱ የፍጥረት ሁሉ መነሻ መሆኑን ስለማያውቁ: እንዴት ብለው ነው የሚቆጣጠራቸው እንዳለ ማወቅ የሚችሉት?
በክርሽና ሁሉም ነገር እንደሚከናወን:እንዴት ነው ለማወቅ የሚችሉት?
ፕራብሁፓድ:አነተ በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዳለህ የምታውቀው እንዴት ነው?እንዴት ታውቃለህ?
ቪሽኑጃን:መንግስት ህግጋቶች አላቸው:ፕራብሁፓዳ:እኛም ህግጋቶች አሉን:
“አናዲ ባሂርሙክሃ ጂቫ ክርሽና ብሁሊ ጌላ አቴቫ ክርሽና ቬዳ ፑራኔ ካሪላ”
ክርሽናን ስለረሳኅው:ክርሽና ብዙ የቬዲክ መፃህፍቶችን ትቶልሃል:
ስለዚህም ብዙ ግዜ ስሜት የማይሰጥን ስነጽሁፎች በማንበብ ግዜያችሁን አታባክኑ እላለሁ
አእምሮአችሁን ወደ ቬዲክ መፃህፍት ማድረግ አለባችሁ:ከዚያም ልትረዱ ትችላላችሁ:
ለምንድን ነው እነዚህ መጽሃፍቶች የቀረቡት? ህጋዊ መሆን እንዳለብን ለማስታዋስ ነው:
ነገር ግን እነዚህን የማንጠቀም ከሆነ ግን:ህይወታችንን እናባክናለን:
ይህ ስብከት የምናደርገው:መፃህፍቶች የምናትመው:ስነጽሁፎች:መጋዚኖች:የክርሽና ንቃተ ማህበራችን:
ይህ ሁሉ እንዴት በአምላክ ቁጥጥር ስር እንዳለን የሚያስታውሰን ነው:ማነው አብይ ተቆጣጣሪው?
እንዴት ህይወታችን ለመበልፀግ ይችላል?ከዚህ አለም ቁጥጥርስ እንዴት መውጣት እንችላለን?
እንዴት ነጻነት ያለው ኑሮ መያዝ እንችላለን?ይህ ነው የእኛ እንቅስቃሴ:
የዚህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴያችን ለዚሁ አላማ ነው:አለበለዛ የዚህ እንቅስቃሴ አላማው ምንድን ነው:
ሌላ “ኢዝም” ለጊዜው ሰውን ለማስደነቅ የተፈጠረ አይደለም:
ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴያችን:የህይወት ችግሮች ሁሉ:መፍትሄ ነው:
ይህ መዘመርም:መልእክቱን የምናገኝበት የልባችን ጎዳና ነው:
“ቼቶ ዳርፓና ማርጃናም” (ቼቻ አንትያ 20 12)ልባችንን ማጠብ ማለት ነው:
ከዚያም ይህ መልእክት ሊደርሳችሁ ይችላል:
የእኛ ስርአትም ሳይንቲፊክ ነው:ስልጣን ያለውም ነው:ይህንን ስርአት የሚከተልም ሁሉ:ቀስ በቀስ ሊረዳ ይችላል:ከዚያም ከፍተኛ ደራጃ ላይ ሊደርስ ይችላል:
ይህ ጥርጣሬ የለውም: