Tip:
Highlight text to annotate it
X
illbehonest.com/amharic
ዋጋውን መመዘን አለባችሁ፣
የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን የሚፈጀውን መጠን ለኩጥ።
መወደድ ይቀራል፣ በስራ ሽግግር ታጣላሁ፣ አንዳንዴም፣
ቀላል ሕይወትን ይቆጥራል፣
እራሳችሁን መቆጣጠር ያስፈልጋል፣ ገላንም መደብደብ ያስፈልጋል።
ምኞትን እንቢ ማለት ያስፈልጋል፣ ዓለምን እንብ ማለት ያስፈልጋል።
ከሕዝብ መገንጠል አለባችሁ።
ለክርስቶስ ለብቻ መቆም ፈቃደኛ መሆን አለባችሁ።
በተለየ የከበሮ ድምጽ ለመራመድ ፈቃደኞች መሆን አለባችሁ።
እና ከሕዝብ መውጥት ማንም ኢየሱስን ባይከተልም።
ማንም በዚህ ዓለም ለኢየሱስ መቆም ባይፈልግ እናንተ ፈቃደኞች መሆን አለባችሁ።
ዋጋው ይህ ነው።
ለክርስቶስ መንገላተት ፍቃደኞች መሆን አለባችሁ፣ እና እንደሚመጣ ልንገራችሁ።
ሕይወታችሁ ሊጠፋ ይችላል።
ጭዋታ ሊጫወት አይደለም የሚመጣው። ዝምተኛ ሊሆን አይደልም የሚመጣው።
ገዢ ሊሆን ነው የሚመጣው። ሊያርድ ነው የሚመጣው።
የነገስታት ንጉስ ነው። የጌቶች ጌታ ነው።
በዓለም ፍጻሜ ድረስ ላይ
እንደ መብረቅ በነጭ ፈረሰ ከሰማይ ይመጣል ልብሱም በደም ይሸፈናል።
በጠላቶቹ ደም። ለማሸነፍ እና ለመፍረድ ተመልሶ ይመጣል።
ከሚመጣው ንጉሥ ጋር መታረቅ በሰላም ስምምነት አለባችሁ።
ያለዚያ የዘላለም ፍርደት ይፈረድባቸዋል።
እና ኢየሱስን ክርስቶስ የሰላም ስምምነትን አሟልቷል።
ከፍርድ ቤት ውጭ መስማማት አለባችሁ።
እስከ የዓለም ፍጻሜ ድረስ ከክርስቶስ ጋር ለመስማማምት መጠበቅ አትመኙ።
ሲፈርድም ምህረቱ ይቀራል።
ነገር ግን ዛሬ ምሕረቱን ይሰጣል።
እጅ እንድትሰጡ እና እንድትገዙ ይፈቅዳል።
የሰላም ስምምነትን ይፈቅዳል ነገር ግን በሱ ፈቃድ ውስጥ ብቻ ነው።
የሱ ፈቃድ ለሰላም ስምምነትን እንደዚህ ነው፥
አባቱንና እናቱን ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ያለዚያ የኔ ደቀ መዝሙር ሊሆኑ አይችሉም።
ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ያለዚህ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
እና ካላረጋችሁ፣ በፍርድ ቀን ላይ እንገናኛለን።
እናንተም ስትጠፉ እግዚአብሔርን ያስከብራል።
እናንተን ወደ ሲሳኔ ጫን ያረጋል። ተስፋ አይቆርጥም።
ካሁን ወድያ ልባችሁን በዝጋት አትችሉም፣ እሱን መመለስ አለባችሁ።
ስለዚህ ባጠቃላይ የሉቃስ ወንጌል 14 ቁ. 33 እንደሚለው፥ «ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።»
የሚለውም ማናያችሁ የእውነት ክርስቲያን ልትሆኑ አትችሉም።
መንግሥቴ ውስጥ ልትሆኑም አትችሉም።
ከኔ ወይም ከአባቴ ጋር ማናችሁም ጥሩ ግንኙነት ሊኖራችሁ አትችሉም።
ማንም ከእናንተ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፥
ያለውን ሁሉ የማይተው።
ጌታችን ምን እያለ ነው? ሀሳቡን አይቀይርም።
በምህራፉ ውስጥ ከቁጥር ወደ ቁጥር የበለጠ ቁርጠኝነት ይጠይቃል።
ወደ መንግስተ ሰማያት ለመሄድ ግዙ ቦታችንን አይደለም የሚለው፣
በቂ ወርቅ ወይም ብር ከኛ ውስጥ ያለው የለም
መንፈሳችን በውስጥ ያቆሸሸውን ኀጢአት ለማጥፋት።
ምን እያለ ነው?
ያለውን ሁሉ የማይተው።
በአገባቡ እና ከሙሉ የእግዚአብሔር ቃል ላይ መተያየት አለበት። እና አባባሉን ማቃለል ይቻላል።
ማዛወር አለባችሁ
ሁሉን ያላችሁን እና የኑሮ ባለቤትነት ወደ እሱ ቀይሩት።
እንደዛ ነው የሚለው።
አሁን ሕይወታችሁ የእናንተ ሕይወት አይደለም፣ የሱ ሕይወት ሆኗል።
ጊዜአችሁ ከአሁን በኋላ የሱ ጊዜ ሆኗል።
ያለን ሁሉ የኛ መሆን ቀርቶ፣ የሱ ሆነዋል።
የወደፊት ያለው ሕይወታችሁ የእናንተ መሆኑ ቀርቶ የሱ ኑሮ ሆኗል።
የእናንተ ሀብት ካሁን ወድያ የእናንተ አይደልም፣ የሱ ሀብት ሆኗል።
ያላችሁን ሁሉ እና የኑሮ ባለቤትነት ወደ እሱ ተላልፏል።
ይህ ነው የሱን የሰላምን ስምምነት ፈቃድን ማሟላት።
ነገር ግን ልውውጡ የሚገዛው በገንዘብ አይደለም ።
የሚገዛው…
ሕይወትን ማስረከብ ለክርስቶስ ለፍፃሜ እና ለመጨረሻ ጊዜ።
ይህ ነው የሚያድን እምነት።
ተስፋ ቆርጠን በሙሉ በሙሉ እምነት።
ያላችሁን ሁሉ እና የኑሮ ባለቤትነት ወደ እሱ ተላልፏል።
የእናንተ የዘላለም ሕይወት። ይህ ብቻ ነው የምትኖሩት ኑሮ።
ይሄ ብቻ ያሳትፋል የዘላለም ሕይወትን።
ስለዚህ እንደዚህ ይላል፥ «ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን…» ምስክር ይሰጣል ማለቱ ነው።
መቼም የእውነት እንዳልሆነ ያሳያል። «በምን ይጣፈጣል?» መልሱ በምንም ነው።
ቁጥር 35፥ «ለምድር ቢሆን ለፍግ መቈለያም ቢሆን አይረባ…»
ለማንም አይረባም፣ ለእግዚአብሔር አይረባም፣ ለክርስቶስ አይረባም፣ ለመንግስተ ሰማያት አይረባም፣ ለእንቅስቃሴው አይረባም፣
የሌላን የወንበር ቦታ ይዛችኋል።
ሌሎች ወደዚህ ለመግባት የሚፈልጉ ነበሩ።
ለምድር አይረባም። ለሽንት ቤትም አትረቡም– በመንፈሳዊ መንገድ ሲታይ።
ለፍፃሜ እና ለመጨረሻ ጊዜ የእናንተን ሕይወት ለማስረከብ የመጣችሁ ስላልሆነ፣
ወደ ክርስቶስ ባለ ከፍተኛ ታማኝነት።
በኢየሱስ ጌትነት በታች አይደላችሁም።
ራሱን ክዶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ።
ከዛም እንደዚህ ይላል፥ «የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።»
እግዚአብሔር በልጁ ያለውን በደንብ በሐሳብ ተረዱ።
እግዚአብሔር በልጁ በዚህ ስብሰባ ላይ ተናግሯል።
እግዚአብሔር ሁላችንም እዚህ ቦታ አምጥቶናል።
በአደጋ ወይም በእድል ማናችንም ዛሬ አልመጣንም፣ የመጣነው በእግዚአብሔር ምህረት እና ቸርነት ብቻ ነው።
እዚህ ቦታ አምጥቶ አሰምቷል ስለ ትንቢተ ኢሳይያስ 53። ስለ አዳኝ ጌታ ኢየሱስን ክርስቶስ ሥቃይ ሰምተናል።
መስቀሉ ላይ ለኛ ብሎ ኃጢያት ሆነ።
መስቀሉ ላይ እራሱ ሞተ እና መኖር እንድንችል።
የኛን ኃጢያትን እና በደልን በዛፍ ላይ ለመሸከም እና ድህነታችንን ለመግዛት እንዲችል።
«መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።»
ኢየሱስም እንዳለው «እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።»
እና ዛሬ እናንተን ይጠራል፥ «ወደ እኔ ኑ።»
«እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ፥ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፥»
«ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።»
«ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።»
ከእናንተ የኃጢአት ሸክም ይነሳል።
አሁን የኢየሱስ ቀንበር ይኖርባችኋል።
ከእናንተ ጋር ቀንበር ተሸክሞ ይጎትታል፣
ነገር ግን በእናንተ ሕይወት ፍጹም የሆነ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል።
ወይኔ፣ እንዴት በዛሬ እለት ልባችንን መመርመር ይገባናል።
ይሄን የፍጹም ቁርጠኝነትን ቦታ ደርሻለው?
ወደ በመስቀል የሞተው የኢየሱስ ገዝነት እና ጌትነት ሕይወቴ ተገዝቷል።
እንድታውቁ እፈልጋለሁ የገነት በሮች ለእናንግተ እንደተከፈቱ።
ጠባቡ ደጅ ክፍት ነው።
የእምነት እርምጃ ከወሰዳችሁ እና በጠባቡ በር(ደጅ) ካለፋችሁ፥
ሕይወታችሁን አስረክቡ ለሱ።
ቃሉም ኮስተር ያለ ቢሆንም።
እንደዚህም ይላል፥ «ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም።»
እንድትመጡ ዛሬ እናንተን ይጠራል፣
ለመምጣት የእምነት እርምጃ እንድትወስዱ።
ነገር ግን ከመጣችሁ…
አትቀልዱ።
ለክርስቶስ ሕይወታችሁን ማስረከብ አለባችሁ።
የተወሰደበር ቪዲዮ «It Will Cost You Everything» ሰባኪው፥ Steve Lawson resolved.org
Steve Lawson የChrist Fellowship Baptist Church in Mobile, Alabama ሰባኪ ነው። cfbcmobile.org
illbehonest.com