Tip:
Highlight text to annotate it
X
ሞተ!
አብ ልጁን ሰጥ።
እንደዚህ ስትሉ፥
«ኢየሱስ ሞተ።» ለአንድ ደቂቃ መገረም አይገባችሁም?
ማለቴ፥ ሞተ። የእውነት ሞተ!
በእንጨት ላይ ነው የእሱ ደም የፈሠሰው፤
በዚህ ምክንያት ብቻ ነው የእኛ የጠቆረው ቆቻቻ ኃጢአት ሊታጠብ የቻለው።
ያኛው ደም በእንጨቱ ላይ የነበረው።
የእግዚአብሔር ልጅ መታረድ።
ሰዉ፣ አምላኩ፣ ሰዉ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ተነሳ።
ከ40 ቀን በኋላ ከአብ በስተ ቀኝ ለመሆን ወደ ላይ ሄደ፣
እና ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ፣
ሰው የመንግሥተ ሰማያት በሮች ፊት ለፊት ቶሞ እንደዚህ ጮኸ፥
«እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።» [መዝሙረ ዳዊት 24 ቁ. 7]
መንግሥተ ሰማያት ውስጥ ያሉት ሁሉ እጅግ ድንጋጤ፣ ዝምታ እና ግርምት ላይ ናቸው።
አንዱ ደፍሮ፥ «ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?» ይላል ።
ማን ነው እንደዚህ ደፍሮ መናገር የሚችለው?
ደፍሮ ማንም በፊት በሩን ሊነካ አይችልም ነበረ።
«ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?»
ከዛም በድንገት ጌታ፣ መሢሕ፣ ክርስቶስ፣
የእግዚአብሔር ልጅ፣ እሱም ለእኛ ይጮኻል፥
«እግዚአብሔር ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ እግዚአብሔር ነው፥ በሰልፍ ኃያል።»
«እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥
የክብርም ንጉሥ ይግባ።»
ለመጀመሪያ ጊዜም፥ ለሰዎች በሮቹ ተከፈቱ።
በበሮቹ ሲያልፍ በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረት ሁሉ በግምባራቸው ወደቁ።
«ሁሉም ይዘምር በኢየሱስ ስም፤
መላክቶች በግምባሬም ይደፋሁ፤ የመንግሥት ዘውድ አምጡ፥ የሁሉም ጌታን የክብር አክሊል አርጉለት።»
«ብዙ አክሊል ስጡት፤
ለበጉ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው።»
ይታየኛል እንዴት ወደ አባቱ በድፍረት…
መብቱ ነበረ… የሰሎሞንን ዙፋን የቀልድ የሚያስመስል ዙፋኑን ደረጃ ሲወጣ፤
ከዛም ሲቀመጥ ፍቃድ ዳይጠይቅ።
አባቱንም ተመልክቶ፣ ፍቃዱን ሳይጠይቅ፥ «አባቴ ሆይ፥ ተፈጸመ!» ይላል።
አባቱም፥ «ልጄ ሆይ፥ የእውነት ተፈጸመ!» ይላል።
እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር የሁሉም ጌታም ክርስቶስም አድርጎታል።
ኢየሱስን ጌታችሁ አድርጉት አልልም፣
እንደዚህ ካልኩኝ ከሁሉም በላይ ሞኝነት ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችሁ ነው!
ቃሉን ባትሰሙ ወይም ብትሰሙም፥ ብትባርኩት፣ ብትረግሙትም፣ ብትወዱትም፣ ብትጠሉትም፥
የእናንተ ጌታ ነው እግዚአብሔር ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ስለሰጠው፥
ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ።
አንዳንድ ባገኙት ጸጋ ምክንያት ይንበረከካሉ፣
ነገር ግን አሕዛብንም በብረት በትር የሚገዛው ሌሎቹም ጉልበታቸውን ይሰብራል።
ስለ እንደዚህ አይነት አምላክ ይቅርታ አልጠይቅም።
ሌሎች ነብያትን ነው የምከተለው፣ በብዛት ሞተው ተቀብረዋል፣
ነገር ግን ሁሉንም እግዚአብሔር በሞተ ወደ ክብር ተቀብሎአቸዋል፤
አይጨነቁም ስለ የሰው አስተሳሰብ እና ስለ የሌሎች ወንጌላዊ ሰዎች አረማመድ።
ስለ በሰማይ ውስጥ ስላለው አምላክ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፣
እና እሱም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል ደግሞ የጠይቃል ከኛ።
በፍቅሩ እና በኃይሉ ፈትዷል
እንድትመጡ ይጮኻል፥ «እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ኑ፥
የተራበው ሁሉ፥ ኑ።
የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ?
ኑ፥ ጠቱ።» ይላል።
«የወይን ጠጅና ወተት።
የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት ምክንያት ለእናንተ ቸርነት አሳያለው።
አሳቤ እንደ አሳባችሁ አይደለም አይደለምና አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
ውኃ ሲፈስበት ዘርንም ስለሚያድግ፥
ከአፌ የሚወጣ ቃሌ የላክሁትንም ይፈጽማል።» [ትንቢተኢሳ 55 ቁ. 1-3፣ 8፣ 10-11]
«ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ።» እያለ ሁላችሁንም እዚህ ያላችሁትን ያዛል። [የማርቆስ ወንጌል 1 ቁ. 15]
«እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት።»
«ወድም ጳውሎስ፥ ልድን እችላለው?»
ይህን አላውቅም።
ጥያቄ ልጠይቃችሁ።
ዛሬ ማታ መጥታችሁ፥
ሰው አመጣችሁ፥ ቁጭ ብላችሁ እስከሚያልቅ ድረስ ትጠብቃላችሁ፣
«መቼ ነው የሚያልቀው?» ትላላችሁ።
አእምሮአችሁ ሌላ ቦታ ነው፣
ድብርት ላይ ናችሁ፣ አሁንም ክርስቶስ ለእናንተ ምንም አይደለም፣ አስተሳሰባችሁ አልቀየረም፣
ስለዚህ ለእናቴ መልሴ «መዳን አትችሉም።» ነው።
አሁን አትችሉም።
ምክንያቱም ልባችሁ ውስጥ ንሰሓ ስለሌለ፥
በኃጢአታችሁ ምክንያት የተሰበረ መንፈስ የላችሁም፥ እንድትኖሩ በተከፈለው ዋጋ ምክንያት የተሰበረ ልብ የላችሁም።
ወይም እንደዚህ እያላችሁ የሆናል፥ «ወንድም ጳውሎስ፥ ዛሬ ስመጣ፥
ለማዳመጥ ፍላጎት አልነበረኝም።»
ነገር ግን ዛሬ ስንዘምር እግዚአብሔር ልባችሁን ነካው እና ወደ ዘላለማዊ ነገሮች ማሰብ ጀመራችሁ፥
ወይም ዛሬ ወንጌል ሲሰበክ ሰማችሁ
ስለ ኃጢአታችሁ ነቃችሁ እና ከቅዱስ አምላክ ፊት እንዴት እርግማን እንደሆናችሁ፥
ነገር ግን ስለ ኢየሱስ ስትሰሙ በልባችሁ ደስ ደስ ካላችሁ
እንደዚህ ካላችሁ፥ «እኔ ከሁሉም በላይ ቆሻሻ ነኝ፥ ተስፋ ለእኔ አለ?»
አዎ፥ ተስፋ አለ ለእናንተ።
ንሰሓ አላችሁ፤ ንሰሓ ይታያል ልባችሁ ውስጥ፤
አንድ የጎደለ ነገር አለ፥ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ እና ትድናላችሁ! [የሐዋርያት ሥራ 16 ቁ. 31]
ትድናላችሁ!
ትድናላችሁ።
«የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።» [Romans 10:13]
«በእርሱም የሚያምን
አያፍርም።» [1 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2 ቁ. 6]
ይሄን እወቁ፥ ጊዜው አጭር ነው፣ ሰዓቱም እያለቀ ነው፣ ሞት እና ገሀነም እየቀረበ ነው።
ክርስቶስ ይመለሳል። ሰዎች የሚሉኝ እንደዚህ ነው፥ «አይጨንቀኝም፥ ለአንድ ሺ ዓመት አይመለስም።»
እውነትም ቢሆንም እናንተ ግፋ ቢል በ25፣ በ50 ወይም በ60 አመት ውስጥ ታዩታላችሁ፣
እዚህ ያላችሁት ሁሉ እሱን ታዩታላችሁ።
እናንተ ወደ እዛ ትሄዳላችሁ ወይም እሱ ወደ እዚህ ይመጣል– ልዩነት የለውም።
ታዩታላችሁ፣ ከእሱ በፊት ትቆማላችሁ።
ይመጣል እና ሲመጣ አስደናቂ እና በጣም የሚያስደነግጥ ይሆናል ።
አንድ ሰባኪ እንዳለው፥ «ጥሩ ዜና እና መጥፎ ዜና አለኝ።
ጥሩ ዜናው፥ እግዚአብሔር እዚህ አለ ነው።
መጥፎ ዜናው፥ እግዚአብሔር እዚህ አለ ነው።»
ቡድናችሁ ነው ዜናውን የሚወስነው።
ይመጣል፥ በድንገት ከሰምይ ይመጣል፣
እና ዓለቶች ጌቶችም በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት ሁሉ ኃይለኛዎችም
ፈረስ የሚጋልበውን አንዴ ሲመለከቱት፣
ተራራዎችን በላያችን ውደቁ ይላሉ።
እወቁ ኀያል እና ገዢ አምላክ፥
ኀያል ሆኖ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ሁሉንም ይገዛል ።
የተፈጠሩት ዓለሞች፣
መላእክት እና ሰዎች ፣ አጋንንቶች እና ዲያብሎስ ከእሱ ጋር ቢዋጉ
ምንም ኃይል አይኖራቸውም፣ ከአንድ ከካማ አይሻሉም።
ትልቅ ድንጋይን በቴስታ ከሚመታ ቁንጥጫ ኃይላችው አይበልጥም።
ይፈረድባችኋል፥
በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም
በእሳት ባሕር ውስጥ ይጣላል። [የዮሐንስ ራእይ 20 ቁ.15 ]
እንደዚህ ሲባል አትመኑ፥ «መንግሥተ ሰማያት ውስጥ እግዚአብሔር ይኖራል፣
ነገር ግን ገሀነም ውስጥ እግዚአብሔር አይኖርም።»
ወገኖቼ፥ ገሀነም ውስጥ እግዚአብሔር ይኖራል።
ገሀነም የእግዚአብሔር ቁጣ እና ፍርጃ ቦታ ነው።
አላነበባችሁም፥
«በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሳቀያል። የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል።» [የዮሐንስ ራእይ 14 ቁ. 10-11]
ሳይጣን አይደለም ገሀነም ውስጥ ገዥ፥ እግዚአብሔር ነው።
የምትሉት፥ «እንደዚህ አይነት ነገር ሰምቼ አላውቀም» ነው።
እውነት ነው፥ ችግራችሁ ይሄ ነው።
ችግራችሁ ይሄ ነው።
ንስሓ ግቡ፣ ወንጌልንም እመኑ።
እኔ አሁን ለእናንተ ማረግ የሚገባኝ፥
ከሰዎች አርቄ ወደ እግዚአብሔር ማስቀረብ ነው።
እስከ ድነት ድረስ እግዚአብሔርን ፈልጉት።
እግዚአብሔርን ፈልጉት።
ጥሩት።
እመኑ በእሱ።
ይህን እወቁ፥
ዛሬ እግዚአብሔር አድኖኛል ብላችሁ ካመናችሁ፥
አንድ ነገር እውቁ፥
በእርግጥ እንደ መዳናችሁን ለማወቅ ዛሬ ብቻ አይደለም የሚያስፈልገው።
ምክንያቱም፥ ዛሬ የዳናችሁ ከመሰላችሁ፥
እና ከዛሬ በኋላ ሕይወታችሁ ካልተለወጠ፤
በጸጋም ካላደጋችሁ፤ እና ፍላጎታችሁ ካልተቀየረ፤
እና ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምታችሁ ካልሆናችሁ፤
ነገር ግን እንደ ብዙ የካዱት ሰዎች ከሆናችሁ፣ ዛሬ የሆነው ለእናቴ ጥቅም እንዳልሆነ እወቁ።
አንዴ ጸሎት በመጸለይ ሰው መዳኑን ማረጋገጥ አይችልም፣
የድነት ማረጋገጫው
ከእሱ ጋር ከቀጠላችሁ ነው፣
እና በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው ይፈጽመዋል።