Tip:
Highlight text to annotate it
X
እኔ ኢንተርኔትን በብዛት እየተጠቀምኩኝ አላደኩም፤ የድሮ ሰው ነኝ።
ቴክኖሎጂ ጥቅም እንዳለው እገምታለው ነገር ግን
በቅርብ እንደጻፍኩት፥ ልቤን ይወጋኛል
ወጣቶች በኢንተርኔት በላይ ሲዋጉ ስለ ትናንች ልዩዩነት በሐይማንቶ ትምህርት ላይ በሚገኘው…
እራሳቸውም ለበቂ ጊዜ አልኖሩም እና ከኑሮም አልተማሩም ስለ የሚከራከሩበት ነገር።
ቁጭ ብለን ኢንተርኔትን በእንደዚህ አይነት ነገር እንሞላዋለን፥
ይሄም መንጌልን ሰምተው የማያውቁ ሺ ሚሊዮን ሰዎች እያሉ።
ያበደ ነገር ነው።
አሁን እኔን እየሰማችሁ ካላችሁ እና ወጣቶች ከሆናችሁ፥
ወጣቶች ከሆናችሁ ለእናንተ ዓለምን መጽሐፍ በመጻፍ ለመቀየሪያ ጊዜ አይደለም፥
ወይም በኢንተርኔት የዓለምን ሕስብ ቡሉም ብታገኙም፥
አሁን ያላችሁ ጊዜ ለመዘጋጀት እና የእግዚአብሔር ሰው ለመሆን ያላችሁ ጊዜ ነው።
ኢንተርኔት ላይ ጊዜ ለማባከን አይደለም፥ ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን ጊዜ ነው፥
መንፈሱን በላያችሁ ላይ እስከሚያወድ እና እናንተን ለመጠቀም እስከሚችል ድረስ።
ከዛም ውኃ አታፍስሱ የበሰበሰና የዘነበበት መሬት ላይ።
ሂዱ ወደ ወንጌልን ሰምተው ለማያውቁት ሰዎች።
ለምንድን ነው በሕይወት የምንገኘው? በዚህ ዓለም ያለው ችግር እና የሚጎድለው ትልቅ ነው…
ነገር ግን ትልቅ ችግር ስላለ እግዚአብሔር ያለ እናንተ ያቅተዋል እና አያሟላውም አልላችሁም።
እግዚአብሔር ያለ እናንተ ሁሉንም መፈጸም ይችላል። ግን እንዴት ያሳዝናል፥ እንዴት ሐዘን ያመጣል።
እናንተን እጋብዛለሁ ወደ ደስ የሚያሰኝና የእውነተኛ መሥዋዕት የሆነ ሕይወት፤ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
እዚህ ያላችሁ አንዳንድ ወጣቶች ወደ እዛ ለመሄድና ወንጌልን ለመስበክ ማሰብ አለባችሁ፥
ለኢየሱስ መሰቃየት እና በስቃዩም መደሰት አለባችሁ።
እኔ 49 ዓመቴ ነው እና አከላተ ወደ ሚሊዮን ቦታ ድቅቅ ብሏል።
እንደ አቶ ሮበርት መሪ ምክሼነን እንዳለው፥ እግዚአብሔር መልክትና ፈረስ ሰጠኝ፥ ፈረሱን ገድያለሁ።
እንደሱ ይሰማኛል ነገር ግን በደንብ ተደስቻለሁ፥ ተደስቻለሁ።
እናንተ ወጣቶች፥ ለእሱ ብለን በንሞት በሞት መከበር ይገባዋል።
ሕይወታችሁን አታባክኑ ለሰው የመንፈሳዊ ትምህርት ዐዋቂ ለመሆን በመሞከር
ከእናንተ የበለጠ እውቀት የሚኖራቸው ይሆናል።
ከዚህ ሄዳችሁ መንጌልን ስበኩ። ወደ ሜዳዎች ሂዱ፤ ወደ ጨለማ ያሉበት ቦታዎች ሂዱ።
የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስበኩት።
እግዚአብሔር ህንድና ነፓል አገር በሰራው ሥራ ምክንያት ምስጋና ላይ ነኝ።
ትቤትም አገር አለ። እግዚአብሔርን ሁሌ እጠይከዋለው፥ መቼ ነው ትቤት ውስጥ ሥራ መጀመር የምችለው?
ቻይና አገር ውስጥም? ሞንጎሊያ አገር ውስጥስ?
ጓደኛዬ ከካሊፎርንያ ክፍለ ሀገር አቶ ላሪ ፔን ኢንተርኔት ላይ ድረ ገጽ አለው፥
ለመታወቅ ቦታ ከምፈልግ ውጭ አገር ውግያ ያለበት ቦታ ብሆን ይሻለናል ይላል።
ወጣቶች፥ እግዚአብሔር እና ገሃነም ብቻ የሚያውቁት ገጠር ሄዳችሁ ሙቱ።
እግዚአብሔር ይወዳችኋልና እናንተ ላይ ያለው መንፈሱ ሲዋጋ ኃይለኛ
ነው ከገሃነም ጋር እና ገሃነም ይጠላችኋል።
የትም ሄዳችሁ ወንጌልን ስበኩ።
እኔ ፒውሪታንስ የሚባሉትን በጣም እወዳለው፥
ማርቲን ሎይድ-ጆንስ እና ቻርልስ ስፐርጄን የምባሉትንም እወዳለው። ከዛም ዘመናው ሰባኪዎችን እመለከታለው
ተባርከናል። አቶ ጆን መካርተር እና አቶ ጆን ፓይፐር እና አቶ ጆል ቢክ …
የሚደነቁ ሰዎች። ዌን ግሩደም እና ብዙ ሌሎች ወንዶች።
የሽመገሉ ናቸው እና ብዙ አጥንተዋል እግዚአብሔር እንዲሰሙም አድርጓል።
ወጣቶች፥ እንደእነሱ ለመሆን አትሞክሩ፥ እስከምታረጁ ጠብቁ።
እስከዚህም አሜሪካ ይፈልገኛል አትበሉ።
አሜሪካ ውስጥ ብሰብክ ተጨማሪ ተረፍ ያለ ሰባኪ እባላለው።
ነገር ግን ሌላ ሰባኪ የሌለበት ቦታ ብሄድ…
እንደኔም ደካማ ብትሆኑም ዋናው ሰባኪ ትባላላችሁ።
አቶ ጆን መካርተር እና አቶ ጆን ፓይፐር የሌሉበት ቦታ ሂዱ፥
እና ወንጌልን ስበኩ እና እግዚአብሔርን ለምኑትና ጸልዩ።
ያነበብቁተን ስለ የሰባኪዎች ስመለከት ሕይወታቸው ውስጥ ጥቂት የሚመሳሰሉ ነገሮች አሉ።
አንዳንዶቹ ካልቫኒስቲክ ነበሩ ሌሎች ደግሞ አልነበሩም።
አንዳንዶቹ የታወቁ ነበሩ ሌሎቹ እንደ ሰማዕት ማንም ሳይታወቁ ሞቱ።
ሁላችሁም የተለያዩ ናችሁ። ነገር ግን አንድ ነገር አግኝቻለው
ሳያቆሙ ይጸልዩ ነበረ።
ጸሎት፤ የታገሰና ትጋት ያለው ጸሎት።
ማንም ስማችሁን ባያውቅ ምን ልዩኑት ያመጣል?
ትክክል ጥያቄው፥ እግዚአብሔር ስማችሁን ያውቃል ወይ? ነው።
ከዛም፥ ጠላታችሁ ስማችሁን ያውቀዋል? የእውነት ይጠላችኋል?
የምትታወቁ ሰባኪ ሆናችሁ ሳይሆን ተንበርክካችሁ በጸሎት ውግያ ላይ ስለሆናችሁ ነው፥
በጉልበታችሁ ላይ ትታገላላችሁ። እሱንም ይዛችኋል።
ጸሎተኞች መሆን አለባችሁ፥ ህንድና ነፓል አገር በጸሎት ብቻ ነው የተቋቋመውና የሚካሄደውም።
ሰምቻቸው የማላውቀው ነገሮች አሉ።
ከቤተሰቡ ጋር ብዙ ጊዜ አጠፋው ብሎ የቆጨው ሽማግሌ አላውቅም።
እንዳውም ተቃራኒ ነገር ነው የሚናገሩት።
ብዙ ጊዜ ጸሎት ላይ የቆየና የሸመገለ ሰባኪ ስለ ጸለየ የቆጨው አግኝቼ አላውቅም።
ነገር ግን በብዛት የማገኛቸው ሰዎች ይቆጫቸዋል በፊት የበለጠ ስላልጸለዩ ።
የእግዚአብሔርን ቃል ወደንብ ካወቃችሁት አስተሳሰባችሁ ትክክል ይሆናል፥
ነገር ግን ለጸሎት የተሰጣችሁ ሰዎች አይደላችሁም፥
ዋጋ የላችሁም እና እንደ ሁለት ሳንቲምም በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ አትጠቅሙም፥
እንደ ሁለት ሳንቲምም በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ አትጠቅሙም።
በእውቀት እና በኩራት የተሞላችሁ ናችሁና ምንም ኃይል የላችሁም።
ምንም ኃይል የላችሁም።
ጸልዩ አሜሪካ ውስጥ ለመታወቅ እንዳትፈልጉ፥
ነገር ግን ለክርስቶስ ስትሞቱ መንግሥተ ሰማያት ውስጥ ስማችሁ እንዲታወቅ።
ጸሎተኛ ወንድ እንድትሆን፥ የእግዚአብሔርን ቃል እንድታጠና፥
ለአዋቂዎች እንድትሰብኩም አይደለም፥
ወንጌልን ሰምተው ለማያውቁት እና በውጭ አገር እግዚአብሔር ላሳደጋቸው ፓስተሮችን፥
ለማጥናት አቅም ያልነበራቸው እንተ እንደነበረህ።
ስብከቴን አዘጋጅቼ አይደለም የመጣሁት። ትላንትና ነው ከህንድና ከነፓል አገር የመጣሁት፥
ጸሎታችሁ ለእኔ ያስፈልገኛል ነገ ወደ ካሊፎርንያ ክፍለ አገር እሄዳለሁ።
እና ስመለስ ለጥቂት ሳምንቶች አርፋለው፥
እዚህ ከHeartCry ጋር እና ከቤተሰቦቼ ጋር፥ ሚስቴና ሦስት ልጆቼ ጋር እቆያለው።
እባካችሁን ጸሎታችሁን እመኛለው። ጸሎታችሁን እመኛለው። አገልግሎቴ በክርስትያኖች ጸሎት የተመሠረተ ነው።
እባካችሁን ጸልዩልኝ፥ ለሁላችንም ጸልዩልን፥
ለህንድና ለነፓል አገር ጸልዩ ለሌሎችም አገሮች ጸልዩ፤
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የክርስቶስ ስም እንዲመሰገን፤
ሙሉ ሽልማት የተሠቃየበትን እንዲያገኝ።
እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ደህና ዋሉ።
ድረ ገፃችንን እዩት heartcrymissionary.com
ስለ የእኛ አገልግሎት መረዳት ትችላላችሁና
ስለ የምናገለግላቸውም ሚሽነሪ የወንጌል መልዕክተኞች መረዳትይ ትችላላችሁ።
"ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናል።" (ትንቢተ ሚልክያ ፩ ቁ. 11)