Tip:
Highlight text to annotate it
X
illbehonest.com/amharic
ከሪዖ ደ ጀኔሮ ከተማ ውች የምትሰራ ሴትዮ ነበረች።
በጣም ድኻ ነበረች፣ ቤቷም የጭቃ መሬት ነበረው።
ስለ ልጇ በጣም ይሰጋት ነበረ፣ ልጇ ቆንጆ ነበረች፥
እና አንድ ቀን ልጇ ቤቷን ትታ እንደምትሄድ ታቅ ነበረ፥
የምትሄድበት ቦታ ሪዖ ደ ጀኔሮ ነበረ፣ ምክንያቱም የተሻለ ኑሬ ለመፈለግ ነበረ፤
ልጇንም ምን እንደሚገጥማት ታውቅ ነበረ።
አንድ ቀን እናቷ ቤት ስትመጣ ልጇ ሄዳ ነበረ።
ጠረጴዛው ላይ ደብዳቤ ነበረ፥ «የተሻለ ኑሬ ለማግኘት ወደ ሪዖ ደ ጀኔሮ ከተማ ሄጃለው።»
እናቷ ታውቅ ነበረ ምን ነገር ልጇን እንደሚገጥማት።
ያላትን ገንዘብ ሁሉንም ይዛ
ወደ ሪዖ ደ ጀኔሮ ከተማ የሚሄድ አውቶቡስ ቲኬት ገዛች፥
ከዛም በኋላ ወደ ፎቶ ቤት ፎቶ ለመነሳት ገባች፥
ብዙ ያላትን ገንዘብ አወጣችው፥ እናትየው የራሷን ፎቶ አስወሰደች።
ከዛም በኋላ ወደ ሪዖ ደ ጀኔሮ ከተማ እናትየው ሄዳ ለጥቂት ወሮች ቆየች።
በየ ሆቴል ፈለገች፣ በየ ምግብ ቤት ፈለገች፣
በየ ፊልም ቤት ፈለገች፣ በየ የጭፈራ ቤቶች ፈለገች፥
በሄደችበት እና በፈለገችበት ቦታዎች ሁሉ የፊቷን ፎቶ ትታ ሄደች።
ከዛም ገንዘቧ ሲያልቅ ወደ ቤቷ ተመለሰች።
በአንድ ቀን ላይ ልጇ የሆቴል ደረጃ እየወረደች ነበረች፥
ከወንድ ልግ ጋር ነበረች።
ሴተኛ አዳሪ ሆና ነበረ፥ በአስራ አምስት ዓመት ያረጀች ትመስል ነበረ፥
ደረጃ እየወረደች ነበረ።
የምትሞት መስሏት ነበረ፥
ነገር ግን ወደ መስታወት ስትመለከት
እንዴት እንዳረጀች ስታይ ሌላ ነገር ታያት።
የእናቷን ፎቶን ተመለከተች፣ ሄዳ ያዘችው እና ማመን አልቻለችም።
ፎቶን ገለበጠችው፥
በስተጀርባ የተጻፈውን አነበበች፥
ይላል እንደዚህ፥ «ግድ የለም ወደ ምንም አይነት ሰው ብትለወጪ
እና ምንም ነገር አርገሽም ቢሆንም ግድ የለም። እባክሽን ወደ ቤት ነይ።»
ስለ የእግዚአብሔር ኃይል አውቃለው፣ ትምህርቶቹን በደንብ አውቃለሁ፥
ትምትቶቹን እቀበላቸዋለሁ።
ስለ መጠራት እና ስለ አስቀድሞም የወሰናቸው ፈቃዶች አውቃለሁ፥ በእነዚህ አይነቶች ትምህርቶች አምናለሁ፥
ነገር ግን አዲሱ ኪዳንን ስንመለከት፥
እግዚአብሔር እንደዚህ እያለ ነው፥
ግድ የለም ወደ ምንም አይነት ሰው ብትለወጡ ወይም ምንም አይነት ነገር ብታረጉም፥
ልጄ መስቀሉ ላይ የሁሉንም ቅጣት ከፍሏል ስለዚህ ወደ እኔ ኑ።
እዚህ ካላችሁት ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ሕይወታችሁን ገና ታበላሻላችሁ።
አንዳንድ እዚህ ካላችሁት ውስጥ የማይጠፋ ጠባሳ አላችሁ፥
በኃጢአትም የመጡ ተባሶች፤
የሞተ ክርስትና ሃይማኖት ብቻ ያያችሁ እዚህም አላችሁ፥
ነገር ግን የሚኖር አምላክን ነው የማመልከው፣ የሚኖርም አዳኝ ልኮልናል።
ስለዚህ ሁሉንም ሰው ከኃጢአቱ ወደ እሱ እንዲመለስ ይጠራል፥
ወደ እሱ የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አይጥልም።
በክርስቶስ እመኑ። እንዴት አይነት ትልቅ አዳኝ ነው።
ታላቂ አዳኝ ነው።
ወደ እሱ እንዳትመጡ ምንም ነገር መንገዳችሁን ላይ አትተዉ።
አንድ ነገረ አለ ከመጠን በላይ የሚያሳዝነኝ፥
ስሰብክ፥ ስለ የእግዚአብሔር ፍቅር ስሰብክ፥
በጣም ለመስበክ ብሞክርም ያሳዝናል፥
በጣም ከባድ ነው ለመግለጽ ለኃጥአተኞች የእግዚአብሔርን ፍቅርን።
እግዚአብሔር ፍቅር ነው!
አዳኝም ሰቶናል።
ስለዚህ ወደ እሱ ካልመጣችሁ በፍጹም የእናንተ ጥፋት ነው።
የዮሐንስ ራእይ 22 ቁ. 17 «…የሚሰማም። ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።»