Tip:
Highlight text to annotate it
X
በመሳጭ የአዲሱ Google ካርታዎች ምስሎች አማካኝነት የእርስዎን ዓለም ያስሱ።
ምስሎችን የሚደርሱባቸው ጥቂት ቀላል መንገዶች አሉ፦ ከፍለጋ ሳጥኑ በታች ያሉ የመረጃ ካርዶች እና
ከማያ ገጹ በታች ያለው ተንሸራታች መስመር።
በመጀመሪያ ማጉያ ይጠቀሙ እና በካርታው ላይ ማንኛውም ቦታ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
የአድራሻ እና የመንገድ እይታ ምስሎች በመረጃ ካርዱ ላይ ይመጣል።
ወደ የመንገድ እይታ ለመግባት ጥፍርአክልን ጠቅ ያድርጉ፣ ከዚያ መዳፊትን ይዘው በመጎተት ወይም አቅጣጫ መጠቆሚያን
በመጠቀም እራስዎን ያመቻቹ።
ከዚያ ሊጓዙበት የሚፈልጉትን መንገድ ብቻ ጠቅ ያድርጉ።
አንድ አካባቢያዊ ንግድ ከመጎብኘትዎ በፊት ሊያዩት ይፈልጋሉ?
ወደ የመንገድ እይታ ዘልለው ይግቡ ወይም «ውስጡን ይመልከቱን» ጠቅ በማድረግ ውስጣዊ ክፍሉን ያስሱ።
ዓለምን በሆነ ሰው አይኖች ለመመልከት ከፈለጉ በካሜራ አዶ የተመላከቱትን በተጠቃሚ
የተበረከቱት ፎቶዎችን ይመልከቷቸው።
እዚያ ላይ አያቁሙ! በአጫውት አዶ የተመላከቱትን አዲሱን የፎቶ ጉብኝቶች ይመልከቱ።
ይህ መሳጭ የ3-ል ተሞክሮ እንደ እርስዎ ባሉ ተጠቃሚዎች በተበረከቱ በመላው ዓለም ዙሪያ ባሉ ከ60,000 በላይ
ታዋቂ ጣቢያዎች ላይ በሚገኙ ፎቶዎች የመነጨ ነው።
በመጨረሻ፣ ወደ የመሬት እይታ በመግባት ከላይ ሆነው ምድርን ያስሱ።
የሚደገፍ አሳሽ የሚጠቀሙ ከሆኑ ህንጻዎችን አጉልተው በ3-ል ሊመለከቷቸው ይችላሉ።
ከታች በስተቀኝ በኩል ያለው የመቆጣጠሪያ ፓነል እይታዎን እንዲያዘነብሉ እና እንዲያሽከረክሩት ያስችልዎታል።
ወይም ደግም እስከመጨረሻው ያሳንሱት.......እና በእይታው ይደሰቱ።
ከአዲሱ Google ካርታዎች ጋር ይተዋወቁ።