Tip:
Highlight text to annotate it
X
ፍቅር በጎ ነገርን ማረግ ብቻ አይደልም። ፍቅር ሕግን ማክበር ብቻ አይደልም።
ፍቅር ከመታገሥ እና ቸርነትንም ከማረግ መላይ ነው፤
እንደዛ ነው ሲራመድ እና ሲናገር፣ ነገር ግን ፍቅር ይሄ አይደልም።
ፍቅር እጅግ ፍላጎት ነው።
ጥያቄ ልጠይቃችሁ፥ ለእግዚአብሔር ፍቅር አላችሁ? እጅግ ትፈልጉታላችሁ?
ለሱ እጅግ ምኞት አላችሁ? አዎ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ልባችን እንደዚህ ላይሆን ይችላል።
አዎ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ መበረታት ያስፈልገናል። ። አዎ፣ ሁላችንም ከጊዜ ወደ ጊዜ
ዓይናችን ይታለላል በማይረባ ነገሮች። አዎ፣ ሁላችን በዚህ እንቸገራለን፣ ነገር ግን
ሰዎች ሕይወታችሁን ሲመለከቱ እንደዚህ ይላሉ ወይ፥ «እጅግ ፍቅር አላቸው፣
ለአገልግሎት ሳይሆን፣ ለራዕይ ሳይሆን፣ ለወንጌላዊ ነገርሮች ሳይሆን፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ነው።»
የእውነት በልባችንን ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥራ የሚገልጠው በድሮ የምንወደውን ኃጢአትን መጥላት
ስንጀምር ነው፣ እና በድሮ የምንጠላውን የጻድቅ ነገርን መውደድ ስንጀምር ነው። መጠየቅ ያለበር ጥያቄ፣ «ተስማምታችኋል ወይ?»
ወይም «ሐሳባችሁ ተቀይሯል ወይ?» አይደለም። ትክክል ጥያቄው እንደዚህ ነው፥ «የእውነት የእናንተ ኑሮ እንደዚህ ነው ወይ?»
እውነት ነው ለእናንተ ወጣቶች፣ ስማግሌዎች እና አሮጊቶች?
የእውነት የእናንተ ኑሮ እንደዚህ ነው ወይ? ለኃጢአት ያላችሁ
ጥላቻ እና ለጽድቅ ያላችሁ ፍቅር እያደገ ነው? ይሄ ነው ትክክል ጥያቄው።
ስለዚህ፥ «በጎ ኑሮ መኖር ትፈልጋላችሁ ወይ?» ብላችሁ አትጠይቁ። እንደዚህም አትጠይቁ፥ «መልካም
መሆን ትፈልጋላችሁ ወይ?» ወይም «ጥሩ ሕይወት አላችሁ ወይ?» ጥያቄ ልጠይቃችሁ፥ «ለእግዚአብሔር ፍቅር አላችሁ ወይ?»
የሚያስጠላኝ ስብከት እንዘዚህ ይላል፥ «አስደናቂ የባለሙያ ሕይወት አላችሁ።
በጣም ቆንጆ ቤት፣ ጥሩ ሥራ፣ ቆንጆ ሚስት
እና በቂ ልጆች አላችሁ። ሦስት መኪኞች አላችሁ እና ጥሩ ስፍራ ውስጥ ትኖራላችሁ።
የሚገርም ኑሮ አላችሁ። ሕይወታችሁ የተሟላ ነው።
አንድ ነገር ብቻ ነው የጎደላችሁ፥ ኢየሱስ ብቻ ነው የጎደላችሁ።» ይሄ ቀፋፊ ስብከት ነው።
ትክክል ስብከት እንደዚህ ይላል፥ «ኑሮአችሁ የማይረባ ነው።
ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ዋጋ የለውም። እሱ የባለሙያ ትርፍ ዕቃ
ሕይወትን ውብ ለማድረግ አይደለም። ከኢየሱስ ጋር ናችሁ፣
እና ኢየሱስም ከእናንተ ጋር ነው ወይም ባዶ የባከራችሁ እና ያልዳናችሁ ናችሁ።»
ጥያቄው፣ «የተሻለው ሕይወት ትፈልጋላችሁ ወይ?» አይደለም። «ወደ መንግሥተ ሰማያት መሄድ ትፈልጋላችሁ ወይ?» አይደለም።
«ጋብቻን ማስተካከል ትፈልጋላችሁ ወይ?» አይደለም። «እነዚህን ሁሉ ትፈልጋላችሁ ወይ?» በፍጹም አይደልም።
እግዚአብሔርን ትፈልጉታላችሁ ወይ? ለእሱ እጅግ ፍላጎት አላችሁ ወይ?
ኃጢአተኞች እንደሆናችሁ ሁሉም ሰው ያውቃል፥ እንዴት እንደሚቀፍ እና ዘግናኝ እንደሆነ
አያውቁም፣ ይህ የሚጠጡትን ማቆም አይፈልጉም፤ ኃጢአትን እንደ ውኃ የጠጡታል።
እንደምታዩት ጥያቄው፥ «ኃጢአተኞች እንደሆናችሁ ይታያችኋል ወይ?» አይደልም።
ጥያቄው እንደዚህ ነው፥ «ይቅርታ፣ ስሰብክልህ
ወይም ጊዜ በጊዜ ስመክርህ፥
እግዚአብሔር ልብን ቀይሮታል ወይ?»
ሰዎች ወደ እኔ እየመጡ፥ «አዲስ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር አለን» ይላሉ። ነገር ግን፣
አዲስ ግንኙነት ከኃጢአት ጋር አላችሁ ወይ? አዲስ ግንኙነት ከኃጢአት ጋር
ከሌላችሁ፣ በፍጹም ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር የላችሁም ማለት ነው!
እግዚአብሔር መንፈሳዊ ሥራ በልባችሁ ውስጥ ሰርቷል ወይ፤
ከዚህም በፊት እግዚአብሔርን የካደ እና የጠላ ኖሩ ነበራችሁ ወይ?
አሁንስ ከሁሉም በላይ በእናንተ ሕይወት ውስጥ እግዚአብሔር ከብሯል እና እሱንም እጅግ ትወዳላችሁ ወይ?
እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው።
የእግዚአብሔርን ሞገስ መንግስተ ሰማያት ውስጥ ለዘላለም ለኛ ይገለጣል።
ብዙ ሰዎች ይህን አይፈልጉም፣ ወንጌላዊ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ያሉትም
አይፈልጉም፣ ይሄንም መግለጽ እችላለው፥ በዚ ጊዜ አይፈልጉትም። አሁን ካልፈለጉት፣
መቼም አትፈልጉትም፣ ምክንያቱም ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚጀምረው ከሞት በኋላ ስላልሆነ ነው።
እንደዚህ ይላል፥ «አንተን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።» ሕይወቱም የሚጀምረውም ልክ
ልባችሁን ካደሰ በኋላ ነው፣ እና የማይረቡ ነገሮችን ይገልፃል።
የጡንቻ ትርዒት በባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በፍጹም የማይረባ ሆኖ መገኘት አለበት።
መንፈሳዊ ትምህርታችን በጣም ምርጥ መሆን አለበት፣ እንዳውም አንዳንዴ እስከ የዩኒቨርሲቲ ደረጃ በድረስ አለበት።
ትክክል ነው ለሰዎች ስለ መንፈሳዊ ትምህርት እና ስለ እውንት ብቻ የምናስብ ቢመስል፣ ነገር ግን
ዘማሪው ሲመራን እጅግ በደስታ እና በደንብ መዘመር ይገባናል!
የእውነት እግዚአብሔርን ትፈልጉታላችሁ?